ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው (BBC interview)

ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው

ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል

የፎቶው ባለመብት,DR. THEODROS W. GEBRIEL

አሁን አሁን የወገብ ህመም አጋጥሟቸው የህክምና ተቋማትን የሚጎበኙ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ለወገብ ህመም የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመለክታሉ። ለመሆኑ ለዚህ መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔውስ?

በዚህ ላይ በፓራጎን የፊዚዮቴራፒና ስፓርት ህክምና ስፔሻሊቲ ልዩ ክሊኒኮች ውስጥ ሥራ አስኪያጅ እና ሜዲካል ዳሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ጋር ቆይታ አድርገናል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ ሦስቱንም ድግሪያቸውን የተከታተሉት በአሜሪካ ሲሆን በፊዚዮቴራፒ በተለይ በስፖርት ህክምና እና ኦርቶፔዲክስ ህክምና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል።

በሙያቸው በአሜሪካ ለ10 ዓመታት የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ላለፉት 12 ዓመታት እያገለገሉ ይገኛሉ።

ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በጥቁር አንበሳ ህክምና ትምህርት ቤት በፊዚዮቴራፒ ዶክትሬት ፕሮግራም በመምህርነት ሠርተዋል።

Presentational grey line

ብዙውን ጊዜ ወጣቶች ለወገብ ህመም ያጋለጣቸውን መንስዔ በውል አያውቁትም። እንዲሁ በደፈናው ድንገት አመመኝ ሲሉ ነው የሚሰማው። ለመሆኑ የወገብ ህመም መንስዔዎች ምንድን ናቸው?

የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎች፣ የምንጫማቸው ጫማዎች ፣ የምንተኛበት ፍራሽ ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፀምበት መንገድ ( Sex position) . . . ለወገብ ህመም ይዳርጉ ይሆን?

ወደዚህ ዝርዝር ከማለፋችን በፊት ስለወገብ እና የወገብ ህመም ምንነት እናንሳ።

ወገብ ቀበቷችን ወይም መቀነታችን የሚያርፍበት የሰውነታችን ክፍል ሲሆን በዚህ ላይ የሚከሰት ህመም የወገብ ህመም ይባላል።

የወገብ ህመም ጽንሰ ሃሳቡ ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም በቀላል አገላለጽ በወገብ አካባቢ በሚገኙ ጡንቻዎች ፣ የነርቭ ሥሮች፣ የአከርካሪ አጥንቶች፣ የጎን አጥንቶች እና ጅማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው። ይህ ጉዳት ጊዜያዊ ወይም ዘለቄታዊ ሊሆን ይችላል።

የወገብ ህመም ዓይነቶች እንደ መንስዔያቸው ይለያያሉ። ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው፦

  • የዲስክ መንሸራተትና መጎዳት፣
  • የአከርካሬ አጥንት አንዱ በአንዱ ላይ መደራረቢያ ክፍል (facet joints) መቁሰልና መድረቅ፣
  • ረዘም ላለ ጊዜ በመቆምና በመቀመጥ የሚፈጠር ከነርቭ መጨፍለቅ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ህመም እና
  • የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛባት የሚከሰት የወገብ ህመም

ከመጨረሻው ነጥብ እንጀምር።

የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛበት የሚከሰተው የወገብ ህመም የሚያጋጥመው ሰውነት በሽታን የሚከላከልበት ሂደት ሌሎች የሰውነት አካላትን ሲያጠቃ ነው። በእንግሊዝኛ አጠራሩ Ankylosing spondylitis á‹­á‰£áˆ‹áˆá¢

የሰውነት የውስጥ ቁስለትን በመፍጠር ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ህመም ነው።

የዚህ ህመም ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል አይታወቅም። በተለይ በመገጣጠሚያዎች እና በአከርካሪ አጥንቶች መጋጠሚያ መካከል ቁስለትን ያስከትላል።

ህመሙ እየጨመረ ሲሄድም የአከርካሪ አጥንቶች እንዲንቀሳቀሱ እንደ ሃዲድ የሚያገለግለው የሰውነት ክፍል ላይ አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸውን ትተው እርስ በእርሳቸው እንዲጣበቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸው ቀርቶ አንድ አካል ይሆናሉ።

በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ማጎንበስ፣ ወደ ኋላ አሊያም ወደ ጎን መንቀሳቀስ አይችልም።

የሌሎቹ የወገብ ህመም ዓይነቶች መንስዔዎችስ?

ለወገብ ህመም የሚዳርጉን መንስዔዎች በርካታ ቢሆኑም ዶ/ር ቴዎድሮስ በ21 ዓመት የህክምና ልምዳቸው የተመለከቷቸውንና ዋና ዋና ያሏቸውን መንስዔዎች ያስረዳሉ።

ከባድ ነገር ማንሳት፡ áˆ›áŠ•áŠ›á‹áˆ ሰው በዕለት ተዕለት ክንውኑ ጥንቃቄ ካላደረገ ወገቡን ሊታመም ይችላል። በባልዲ ውሃ ቀድቶ ፎቅ ላይ መውሰድ፣ ክብደት ያላቸውን ሰዎች ከአልጋ ማንሳት እንዲሁም ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ ክብደትን ማንሳት ለወገብ ህመም ሊዳርግ ይችላል።

ከልክ በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት መኖር፡ á‰ á‰°áˆˆá‹­ በአንድ ጊዜ የሚጨምር የሰውነት ክብደት የወገብ ህመም እንደሚያስከትል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት አካላዊ እንቅስቃሴ የሌለው ሥራ በመዘውተሩ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ተበራክቶ ነበር" ይላሉ።

ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ፣ ተቀምጦ ወይም ቆሞ ጎንበስ ብሎ መስራት፡ áˆ¨á‹˜áˆ ላለ ጊዜ ቆመው፣ ተቀምጠው አልያም ቆመው ከአንገታቸው ተጎንብሰው በሚሰሩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለወገብ ህመም የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አንድ ሰው ቆሞ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ በሚሰራበት ጊዜ በሁለት አከርካሪ አጥንቶች መካከል ወደ 270 ኪሎ ግራም ግፊት እንዳለው ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። ይህን በየቀኑ ማድረግ ደግሞ ከጊዜ በኋላ የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ብዙ ጊዜ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች በዚህ ሳቢያ ለሚከሰት የወገብ ህመም ሲጋለጡ ይስተዋላል።

ብዙ መንገጫገጭ ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር፡ á‰¥á‹™ ንዝረት ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር ወይም ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ላይ መኪና ማሽከርከር ከጊዜ በኋላ የወገብ ህመም ያስከትላል።

የዝላይ እና የሩጫ እንቅስቃሴዎች፡ á‰ á‰°áˆˆá‹­ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ሩጫ ወይም የመዝለል እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወገባቸው ሊጎዳ ይችላል።

እንደ አስፓልት ያለ ጠንካራ የሆነ ቦታ ላይ የሚሮጡ ሰዎችም መሬቱ ላይ እግራቸውን በጣሉ ቁጥር መሬትም በአጸፋው ስለሚመታቸው ለጉዳት ሊዳርጋቸው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጣ ገባ የሆነ መሬት ላይ የሚሮጡ ሰዎች እግራቸው በሚያርፍበት ሰዓት ሚዛናቸው እኩል ስለማይሆን ወገብ ላይ ጫና ይፈጠራል።

ሰውነት ሳይለምድ በአንድ ጊዜ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት፡ áŠ áˆáŠ• አሁን በወጣቶች ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎችንም ዩቲዩብ በማየት የሚመርጡም አሉ።

ይህ ብቻም ሳይሆን ስፖርቱን ለምን ዓላማ እንደሚሰሩ የማያውቁ በርካቶች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ተጎድተው ወደ ክሊኒካቸው የሚመጡ ወጣቶች መኖራቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ።

"ችግሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ የተከሰተ ሳይሆን ሰውነት ሳይለማመድ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት ነው" ይላሉ።

"ጂምናዚየም ውስጥ ለአሰልጣኝ ጉርሻ መስጠት የተለመደ ሆኗል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንድ አሰልጣኞች ጉርሻዋን ለማግኘት ደንበኞቻቸው የሚፈልጉት የሰውነት ለውጥ ላይ ቶሎ ማድረስ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። አሰልጣኞቹ ስለስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንጂ ስለጤና እውቀት ላይኖራቸውም ይችላል።

አንዳንድ ሰልጣኞችም በአንድ ጊዜ በሰውነታቸው ላይ የሚፈልጉት ለውጥ እንዲመጣ ባልተገባ መልኩ ከልክ በላይ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ።

ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን ሲገልጹት "ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጎ የማያውቅ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ጂምናዚየም ገብቶ አገር ይያዝልኝ እንደ ማለት ነው" ይላሉ።

የወገብን ውስጣዊ ክፍል የሚያሳይ ምሥል

የፎቶው ባለመብት,GETTY IMAGES

ዲስክ መንሸራተት፡ á‹¨á‹²áˆµáŠ­ መንሽራተት ስሙ ለብዙዎቻችን ጆሮ እንግዳ አይደለም።

ዶ/ር ቴዎድሮስም የዲስክ መንሸራተት ያለ ስሙ ብዙ ስም የተሰጠው በሽታ ነው ይላሉ።

ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት የዲስክ ችግር ተብለው ወደ ክሊኒካቸው ከሚመጡት 100 ሰዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ችግራቸው ሌላ ነው።